ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃም ሆትስፐርን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃም ሆትስፐርን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ- ግብር ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየሞ በተካሄደው ጨዋታ ኢስማይላ ሳር በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ጆርዳን ስትራንድ ላርሰን ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ዶምኒክ ሶላንኬ ለስፐርስ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
የቶተንሃሙ ተከላካይ ሚኪ ቫን ዴቬን በ38ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
የተጫዋቹ ከሜዳ መውጣት በቶተንሃም የጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል።
በቡድናቸው ብቃት ያልተደሰቱት የቶተንሃም ደጋፊዎች ጨዋታውን አቋርጠው ከሜዳ ወጥተዋል።
በሊጉ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። የሰሜን ለንደኑ ክለብ ባለፉት 11 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
አዲሱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በሶሶት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ በ38 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል።