የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ላይ ለሚቃጣ ጥቃት በጋራ እንደሚመክቱ ያሳዩበት ነው - ኢዜአ አማርኛ
የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ላይ ለሚቃጣ ጥቃት በጋራ እንደሚመክቱ ያሳዩበት ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፡- የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን በውስጥ ችግሮች ውስጥ ሆነው እንኳ በሀገራቸው ላይ ለሚቃጣ ጥቃት በኅብረት እንደሚመክቱ ለዓለም ያስመሰከሩበት ታሪካዊ ድል መሆኑ ተገለጸ።
"በካራማራ ያገኘነው ድል በቀይ ባሕር ይደገማል" በሚል መሪ ሐሳብ 48ኛው የካራማራ የድል ቀን ተከብሯል።
የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ በዚሁ ወቅት፤ የካራማራ ድል የኢትዮጵያ ልጆች የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ያስከበሩበት የ“ዳግማዊ ዓድዋ” ተምሳሌት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በውስጥ ችግሮች ቢሆኑም እንኳ በሀገር ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ጥቃት በጋራ እንደሚመክቱ ለዓለም ያስመሰከሩበት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የአሁኑ ትውልድም በልማትና በሀገር ጥቅም ማስከበር ረገድ ዝግጁ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸው መግለጻቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ መረጃ አመላክቷል።
በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ቪልማ ቶማስ በበኩላቸው፤ የካራማራ ድል በኢትዮጵያና በኩባ መካከል ያለውን የረጅም ወዳጅነት ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑን ጠቅሰዋል።