በከምባታ ዞን የተገነባው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
በከምባታ ዞን የተገነባው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
ወንጀላ፤ የካቲት 26/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የወንጀላ ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
በዞኑ ዶዮገና ወረዳ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ናቸው።
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባ ሲሆን ከ7 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ 1ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ጋን እንደተገነባለትም በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ከመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተጨማሪ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በክልሉ መንግሥት የተገነቡ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በልማት ፕሮጀክቱ የምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ እና ሌሎች የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።