ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መንገድ ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ሀብታሙ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አንዋር በድሩ እና ሩዋንዳዊው ፓትሪክ ሲቦማና ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ይገዙ ቦጋለ የአርባምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከስድስት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ16 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።


 

በሌላኛው መርሐ-ግብር ወላይታ ድቻ እና ሃዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቴዎድሮስ ታፈሰ ለወላይታ ድቻ፣ ብሩክ ታደለ  ለሃዋሳ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ23 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ሃዋሳ ከተማ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት የማጥበብ እድል አልተጠቀመበትም።


 

ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና ባህርዳር ከተማን 2 ለ 0 ረቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም