ቀጥታ፡

ዎልቭስ ሊቨርፑልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዎልቭስ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሞለኒው ስታዲየም  በተካሄደው ጨዋታ ሮድሪጎ ጎሜዝ በ78ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ዎልቭስን መሪ አድርጋለች።

መሐመድ ሳላህ በ83ኛው ደቂቃ የሊቨርፑልን የአቻነት ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል አንድሬ በ94ኛው ደቂቃ ለዎልቭስ የአሸናፊነቱን ጎል አስቆጥሯል።

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ዎልቭስ በ16 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።

በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ48 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።



በሌሎች የ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኤቨርተን በርንሌይን 2 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።



ቦርንማውዝ እና ብሬንትፎርድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም