ቀጥታ፡

የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ልማት ይገባዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ልማት ይገባዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም የትግራይ ህዝብ ለሰላም እና ልማት የታገለ መሆኑን ጠቁመው፤ የሰላም እና ልማት ፍላጎቱ ትልቅ መሆኑንም ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ዕረፍት ይፈልጋል፤ ሰላም ይፈልጋል፤ ልማት ይፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ክልሉ በሁሉም ክልሎች እየመጣ ያለው ልማትና ሰላም እንደሚገባው ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ደግሞ በአረጀ አስተሳሰብ ሊረጋገጥ አይችልም ብለዋል።

በእርጅናቸው ጊዜ ጦርነት የሚቀሰቅሱትን ደግሞ ተዉ ሊባሉ እና የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

መንግስት የህዝቡን ፍላጎት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ነው ጨምረው የገለጹት።

ከሰላም ፈላጊዎች ጋር፤ ከተማሩ ወጣቶች ጋር ተባብረን ለትግራይ ክልል ሰላምና ልማት እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም