ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ከመቻል ሃዋሳ ከተማ ከባህርዳር ከተማ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 24 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከመቻል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሸገር ከተማ በሊጉ ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች መካከል 10 ጊዜ ሲያሸንፍ፤ በአምስቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በጨዋታዎቹ ላይ 24 ግቦችን ሲያስቆጥር 16 ጎሎችን አስተናግዷል። 

አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ30 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው መቻል በውድድር ዓመቱ 15 ጨዋታዎችን አከናውኖ፤ በዘጠኙ ድል ሲቀናው ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ አራት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። 24 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ስምንት ጎሎች ተቆጥረውበታል።

መቻል በ31 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።  

ሸገር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ፤ መቻል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። 

በሌላኛው መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ ከባህርዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሃዋሳ ከተማ እስከ አሁን በሊጉ 15 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን> ስምንት ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በአምስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 

በ15ቱ ጨዋታዎች ላይ 24 ጎሎችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፤ 11 ግቦችን አስተናግዷል። ቡድኑ በ29 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። 


 

ባህርዳር ከተማ በበኩሉ ካከናወናቸው 15 ጨዋታዎች መካከል ሶስት ጊዜ ድል ሲቀናው፤ 11 ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ አንድ ጨዋታ ነጥብ ጥሏል። ስምንት ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ጎሎች ተቆጥረውበታል። 

ቡድኑ በ10 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ከቀኑ 7 ሰዓት አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ዘጠነኛ፣ ሲዳማ ቡና በ18 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዘዋል። 

ሁለቱም ቡድኖች በ15ኛ ሳምንት ካጋጠማቸው ሽንፈት አገግመው ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም