የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ዎልቭስ ሊቨርፑልን በሞልኒው ስታዲየም ያስተናግዳል።
ዎልቭስ በ13 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በ48 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ጨዋታው ዎልቭስ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ እና ከወራጅ ቀጠና የመውጣት ተስፋውን ለማለምለም የሚያደርገው ነው።
ሊቨርፑል ካሸነፈ በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዝገባል። በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ሶስት ነጥብ ማግኘት ወሳኝ ነው።
የ36 ዓመቱ ቶማስ ብራሞል ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቦርንማውዝ ከብሬንትፎርድ፣ ኤቨርተን ከበርንሌይ እና ሊድስ ዩናይትድ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።