ቀጥታ፡

ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጉባ፤ ዐድዋ በልኩ ሲዘከር!

የዐድዋ ድል የጦር ሜዳ ድል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በራሷ እንደምትወስን ለዓለም የታወጀበት አዋጅ ነበር።

መስዋዕትነታቸውን የምንዘክረው በትላንትናው ግርማ በመኖር ብቻ ሳይሆን፣ የዛሬውን አሻራችንን በመገንባት ነው። በዐድዋ መንፈስ እየተመራን የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ መቅረጻችንን እንቀጥላለን። 

ከዐባይ ወንዝ የተነሳው 'ሁለተኛው ዐድዋችን' ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ያለፈውን ዘመን የምንዘክረው የአሁኑን ጊዜ በአሸናፊነት በመምራት መሆኑን ሕያው ምስክር ነው።

መደመርን ባነጸው በዐድዋ መንፈስ ስንመራ ሀገራችን የማታሳካው አንዳች ነገር አይኖርም። በአንድ ዓላማ በመሰለፍ በመደመር ስንጓዝ የኢትዮጵያ አቅም ከቶ ሊገታ አይችልም።

ታላቅ የነበርን፤ ይበልጥም ታላቅ እንሆናለን!

#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም