ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት ስር የመታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።


 

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች 130ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት እና በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።


 

ኢትዮጵያውያን የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ሀገራቸውን ቅኝ ሊገዛ የመጣውን ወራሪ በኅብረትና በጀግንነት በማሸነፍ ያስመዘገቡት የዓድዋ ድል የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ያስጠበቀ፣ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንዲል የሆነ ሕያው ድል ነው።

#አድዋ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ENA #Ethiopian_News_Agency

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም