የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ1447ኛው የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሂዷል።
''አብሮነትና በጎነት በረመዳን'' በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ ረመዳን ሕዝበ ሙስሊሙ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በመሰባሰብ የሚረዳዳበት የአብሮነት ወር መሆኑን ገልጸዋል።
ባንኩም ይህንን መንፈስ በመጋራት አብሮነትና አንድነትን ለማጠናከር የኢፍጣር መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
በቀጣይም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በማጠናከር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።