ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከተማን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  21ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብርሃኑ በቀለ እና መስፍን ታፈሰ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ተባረክ ሄፋሞ ለሃዋሳ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሲዳማ ቡና በ39 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። በሊጉ 10ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ36 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ጨዋታውን ተከትሎ 21ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም