ቦርንማውዝ እና ሰንደርላንድ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ቦርንማውዝ እና ሰንደርላንድ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ቦርንማውዝ እና ሰንደርላንድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በቫይታሊቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤሊዘር ማዬንዳ በ18ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ሰንደርላንድ መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ኢቫኒልሰን በ64ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ቦርንማውዝን አቻ አድርጋለች።
ባለሜዳው ቦርንማውዝ በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ቡድኖቹ ተመጣጣኝ ሊባል በሚችል ሁኔታ ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን አድርገዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ቦርንማውዝ በ39 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ቦርንማውዝ ባለፉት ሁለት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።
ሰንደርላንድ በ37 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።