ዎልቭስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ዎልቭስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ዎልቭስ አስቶንቪላን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሞልኒው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ጎሜዝ በ61ኛው እና ሮድሪጎ ጎሜዝ በ98ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በጨዋታው አስቶንቪላ ብልጫ ቢወስድም ዎልቭስ ያገኛቸውን ግልጽ እድሎች ወደ ግብ በመቀየር ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ዎልቭስ በ13 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
ላለመውረድ የሚያደርገውን ትግል የሚያግዝ ድል አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ሻምፒዮንስ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።