ማንችስተር ሲቲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በኢላንድ ሮድ ስታዲየም ይጫዋታሉ
ሊድስ ዩናይትድ በ31 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ማንችስተር ሲቲ በ56 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ውሃ ሰማያዊዎቹ አራተኛ ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዘገብ ይጫወታሉ።
በ27ኛ ሳምንት ከሜዳው ውጪ ከአስቶንቪላ ጋር አንድ አቻ የተለያየው ያሸነፈው ሊድስ ዩናይትድ ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ ይፋለማል።
ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ሊቨርፑል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ዌስትሃም ዩናይትድን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ያስተናግዳል።
ሊቨርፑል በ45 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ዌስትሃም ዩናይትድ በ25 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ጨዋታው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ደግሞ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ሶስት ነጥብ ለማግኘት የሚፋለሙበት ነው።
ቼልሲ ከበርንሌይ እና ብሬንትፎርድ ከብራይተን በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ኒውካስትል ዩናይትድ ከኤቨርተን እና በርንሌይ ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ቦርንማውዝ ከሰንደርላንድ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 በቫይታሊቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።