ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናወኑ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከአዘርባጃን ፕሬዝደንት ኢልሃም አልየቭ ጋር ከሚያደርጉት ውይይቱ ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይ እና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።


 

እነዚህ ሀውልቶች የህዝቡን የማይበገር አንድነት የሚወክሉ ሲሆን፤ ለአዘርባጃን አንድነት መስዋዕትነት ለከፈሉ ሁሉ ያለንን ጥልቅ ክብር መግለጽ እንወዳለን ሲልም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም