ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል።
ይኅው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያስታወቀው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውም ተገልጿል።
በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።