በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊርማዬ ከበደ እና ፍሬነሽ ዮሐንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ብሩክታዊት አየለ የአዲስ አበባ ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
የድሬዳዋ ከተማዋ ፍሬነሽ ዮሐንስ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ በ19 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባህርዳር ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።