ወላይታ ድቻ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ካርሎስ ዳምጠው ግቦቹን አስቆጥሯል።
የድሬዳዋ ከተማው ድልአዲስ ገብሬ በ51ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ በ22 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በሊጉ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ25 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሐ ግብር አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።
ለአዳማ ከተማ አላዛር ሽመልስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አህመድ ሁሴን ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጀቤሳ ሚኤሳ እና ቢንያም ፍቅሩ በጨዋታ ሄኖክ አዱኛ በፍጹም ቅጣት ምት ለሸገር ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አዳማ ከተማ በ32 ነጥብ አምስተኛ፣ ሸገር ከተማ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘዋል።