በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባህርዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊድያ ጌትነት በ47ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራች።
የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ባንቺይርጋ ተስፋዬ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ40 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከተከታዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህርዳር ከተማ በ10 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።