ቀጥታ፡

ለብሔራዊ ጥቅም መቆም ለዘመናት የቆየ የአብሮነትና የሀገር ፍቅር ውጤት ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)ለብሔራዊ ጥቅም መቆም ለዘመናት የዳበረ የአብሮነትና የሀገር ፍቅር ውጤት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

130 የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ፣ "ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።


 

በዚህ ወቅት ቢሮ ሀላፊዋ እንደተናገሩት የአድዋ ድል የሀገራችንን ዕጣ ፈንታ የሚቀይር፣ አንድነቷ የጸና እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያነሳሳ ነው

የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅም የዚሁ "ዳግማዊ አድዋ" ህያው ማሳያ እንደሆነና ለሌሎች ሁለንተናዊ ስኬቶች መነሳሳት እንደሚሆን ተናግረዋል

የዘንድሮው 130ኛው የአድዋ ድል በዓል በዋናነት በይቻላል መንፈስ ውጤቶቻችንን እና መልካም ገጽታችንን ለዓለም ያሳየንበት፣ በንጋት ሃይቅና በጉባ ተራሮች ላይ የብልጽግና ብስራቶችን ያወጅንበት እና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚከናወንበት ወቅት ላይ መሆናችን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።


 

በውይይቱ ላይ "የአድዋ አደራ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ማንሰራራት!" በሚል የመወያያ ሰነድ መቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል


 

በመድረኩመከላከያ ሰራዊት የዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል በላይ ስዩም፣ የአድዋ ድል በዓል የነጻነት ተምሳሌት በመሆኑ ትውልዱ ታሪኩን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አለበት ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባስተላለፉት መልዕክት የህዳሴው ግድብ ዳግማዊ አድዋ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም