ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የስኬት ጉዞ …

(በሙሴ መለሰ)

ኢትዮጵያ በየዘርፉ እያስመዘገበቻቸው የሚገኙት ስኬቶች በተለያዩ የዓለም መድረኮች ምሳሌነት እያስጠቀሳት ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በአምስቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አምዶቿ ማለትም በግብርና፣ በኢንዳስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ቀጥለን እንዳሥሣለን።

  • የስንዴ ምርታማነት ስኬት

ኢትዮጵያ በግብርና በተለይ በሌማት ትሩፋት እና በስንዴ ልማት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ስኬት ያስመዘገበችባቸው መስኮች ናቸው። ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ታወጣ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከለውጡ መንግስት ወዲህ ግን በተለይ ለስንዴ ልማት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የግብርና ሜካናይዜሽን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን በከፍተኛ መጠን ማሳደግ በመቻሉ ከራስ ፍላጎት ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ ትገኛለች። ይህ ውጤታማነቷም በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጭምር እውቅና አስችሯታል።

ለስንዴ ምርት እና ምርታማነት ማደግ ዘመናዊ የመስኖ ሥርዓቶች፣ የኩታ ገጠም አስተራረስ ዜዴ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን ስልቶችና የግብርና ኢኒሼቲቮች በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

በዚህ መነሻነት ነው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት ለአፍሪካ አርዓያነት ያለው መሆኑንና በስንዴ ልማት ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበችው ለውጥ ከፍተኛ መነሳሳት መፍጠሩን ጠቅሰዋል።

ይህን የኢትዮጵያን ውጤታማነት መነሻ በማድረግም የአፍሪካ ሀገራት እንዲተገብሩት መክረዋል።

በተመሳሳይ በ2016 . ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ መሸለማቸው ይታወቃል።

ሽልማቱ በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ትጋት፣ ፈጣን፣ ተለዋዋጭና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው።

የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት ስኬት የግብርናው አብዮት ማሳያ ሲሆን፤ ራስን መቻል እና ለአፍሪካ መብቃትን ያለመ ነው።

  • ዲፕሎማሲያዊ ስኬት  


 

በሰላም ግንባታ፣ ግጭት አፈታት እና አኅጉራዊ ትሥሥር ረገድ ሚናዋን እየተወጣች ያለችው ኢትዮጵያ፤ በዲፕሎማሲው መድረክም ተደማጭነቷ እያደገ መጥቷል። በሰላም ማስከበር፣ አረንጓዴ ዐሻራና በሌሎች ዐበይት ጉዳዮች ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት በዓለም መድረኮች ስሟ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው።


 

የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን፣ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶየቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ፣ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው፣ የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የሌሎች ሀገራት ባልሥልጣናት የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝቶች የሀገሪቱን የጂኦ ፖለቲካዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ብሎም የዲፕሎማሲ ተደማጭነት እያደገ መምጣት ያሳያሉ።

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ በዓለም መድረክ የአፍሪካ ድምጽ እየሆነች ትገኛለች።


 

  • አረንጓዴ ዐሻራ - ሌላኛው የኢትዮጵያ ስኬት   

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሐምሌ 2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርእስከአሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። 2011 . 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፤ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ በተከናወነው ሥራ አሁን ላይ ከ23 በመቶ በላይ ደርሷል።

በኢትዮጵያ በተካሄደው 2ኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራው ዕውቅና ተችሮታል። በተጨማሪም በ2ኛ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ የአረንጓዴ ዐሻራራዋን ኢትዮጵያ ባስተዋወቀችበት ወቅት፤ የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ መሆኑንም በምሳሌነት ጠቅሰውታል።

ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ችግኝ በመስጠት የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን አሳይታለች። ይህም "አረንጓዴ ዲፕሎማሲ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትን ለማዳበር አስተዋጽኦ አበርክቷል።


 

  • የግዙፍ (ሜጋ) ፕሮጀክቶች ግንባታና ምረቃ

በወርሃ ጳጉሜን 2017 . በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የኢነርጂ ትሥሥር ውጥን ትልቅ የምሥራች ነው። የጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ የሚያገኙት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትም ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግር የሕዳሴ ግድብ የአፍሪካ ራስን የመቻል ምልክት እና የኢትዮጵያ አይበገሬነት ተምሳሌት መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/)፤ የኒውክሌር ማበልጸጊያ እንደሚገነባ፣ የጋዝ ፋብሪካ እንደሚመረቅ፣ የነዳጅ ማጣሪያ ዕውን እንደሚሆን በአፍሪካ ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚገነባ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታ እንደሚከናወን ጉባ ላይ ማብሠራቸው ይታወሳል።


 

ይህን ተከትሎም በሶማሌ ክልል የጋዝ ፋብሪካ ተመርቋል፣ የቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታተጀምሯል። የሌሎች መሠረተ ልማቶች ግንባታ እና የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

እየተገነባ ያለው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለኢነርጂ አቅርቦት ዕድገት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት መገለጹ ይታወሳል።


 

  • የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማዘመን ሥራዎች

የኮሪደር ልማት ኢኒሼቲቮችትራንስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንዲዘምኑ፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ፣ የንግድ ተቋማት አሰራር እንዲዘምን፣ አምፊ ቴአትርን ጨምሮ የኪነ-ጥበብ መሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ግንባታ እንዲከናወን የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ የክልል ከተሞችን ከማስዋብ ባለፈ ዜጎች በንጹህ አካባቢ እንዲኖሩ አስችሏል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ .. 2025 ስለ አዲስ አበባ ሲናገሩ፤ ከተማዋን ጊዜ ወስደው መመልከታቸውንና ከፍተኛ መሻሻል እንዳዩ መግለጻቸው አንዱ ማሳያ ነው

የኬንያ የፓርላማ አባል ጁኔት መሐመድም አዲስ አበባን የአፍሪካ አዲሷ ዱባይ ሲሉ አድንቀው፤ አዲስ አበባ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ምሳሌ መሆኑንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ዲፕሎማቶች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲሁም የልማት አጋሮች ለአዲስ አበባ የከተማ መዘመንና ለውጥ ምስክርነታቸውን መስጠታቸው አይዘነጋም።


 

  • በሰው ሠራሽ አስተውሎት ረገድ

ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከአምስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቁማ ወደ ሥራ ገብታለች። በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠም ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75 ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ ባካሄደው መድረክ ላይ፤ ፈጥነን ልጆቻችንን ካዘጋጀን ሰው ሠራሽ አስተውሎትን እንደ ተለያዩ ምርቶች በቀላሉ መጠቀም እንችላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የምትገነባው የኤ አይ ዩኒቨርሲቲም የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ብዙ ችግሮችን ይፈታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረት እየጣለች መሆኗንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዘመኑን የዋጀ ዕይታ ለዲጂታል ዘመን ለውጦች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንም ይፈጥራል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና ኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያን በዲጂታል ዘርፉ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የማሸጋገርቅም አላቸው።


 

  • ኢትዮጵያ - የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል

የአፍሪካ አቪዬሽን ምልክት የሆነው ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ኢትዮጵያን ከቀሪው ዓለም እና አፍሪካን ርስ በርስ በማገናኘት በኩል የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ነው።

የአየር መንገዱ የመንገደኞች እና የካርጎ አገልግሎቶች የንግድ፣ የቱሪዝም እና ዓለምአቀፍ የቢዝነስ ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተም ይገኛል። በተያዝው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽም አየር መንገዱ 10 ነጥብ 64 ሚሊየን ሰዎችን ማጓጓዝ መቻሉ ለመሪነቱ ትልቅ ማሳያ ሆኖ ይወሰዳል።

በሌላ በኩል በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው ቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀምሯል። የዚህ  ግንባታ መጀመር ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን የመሪነት ሚና አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁነኛ ሚና አለው


 

  • ሌላኛው የኢትዮጵያ ስኬት - ቱሪዝም

ኢትዮጵያ በታሪክ፣ ባህል፣ በተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች የታደለች ናት። እነዚህም ጎብኚዎችንና ተመራማሪዎችን መሳባቸውን ቀጥለዋል።

መንግሥት እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ ወስዶ እየሠራበት በሚገኘው የቱሪዝም ዘርፍ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) ሐሳብ አመንጪነት፤ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታትውልድ አማካኝነት የተከናወኑ ሥራዎች የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እያሳደጉም ይገኛሉ።

በቅርቡ በሶማሌ ክልል የተመረቀው እና የገበታ ለትውልድ ሥራ አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት የዚሁ ሥራ ማሳያ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በምረቃው ወቅት፤ ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምሥራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ሥራ ነው ማለታቸው ይታወሳል

በአዲስ አበባ የሚገኙት የወዳጅነት ዐደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና ሌሎችም ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሆነዋል። የኮሪደር ልማቱም የመዲናዋን መልክ በአዲስ ሁኔታ በመግለጥ ጎብኚዎችን እየሳበ ነው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በግብርና፣ዲፕሎማሲ፣ኢኖቬሽን፣መሠረተ ልማት፣ በከተማ ማዘመንና ኮሪደር ልማት፣ ቱሪዝምን ጨምሮ በሌሎች መስኮች ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች የራሷን መጻኢ ጊዜ ብሩኅነት ያመላክታሉ።

የኢትዮጵያ ስኬቶች ብሎም ስትራቴጂካዊ ራዕይዜውን የሚመጥን ዕድገትን በትጋትና በጋራ ትብብር የመሥራት ውጤትን የሚያሳዩ ናቸው።

ኢትዮጵያ ለዛሬ ብቻ እየሠራች አይደለም፤ ቀጣይ ለሚመጡ ትውልዶች መሠረት እየጣለችም እንጂ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም