ቀጥታ፡

ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ግብዓት ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018(ኢዜአ)፦ ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የህክምና ግብዓት ድጋፍ ተደረገለት፡፡

ድጋፉን ያደረገው ኦርፋንስ ኢንኒድ ዩኤስኤ /Orphans In Need USA/ የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ድጋፉ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ በኩል የተገኘ መሆኑም ታውቋል፡፡

የህክምና ግብዓቱ ለተለያዩ ህክምና አገልግሎቶች የሚውልና ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ካሊድ ሸረፋ ገልጸዋል፡፡

የህክምና ግብዓቱ ከአንድ ሺህ በላይ አይነት እንደ ጠቅላላ ቀዶ ህክምና፣ የአጥንት ህክምና፣ የእናቶችና ህጻናት እና ሌሎች ህክምናዎች እንደሚውል ተገልጿል።


 

ድጋፉ ከስልሳ ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ እንዳለውም የፋርማሲ ዳይሬክተሩ ሀቀዲን ከድር ገልጸዋል፡፡

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባላትና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የህክምና ግብዓቱ ርክክብ ተከናውኗል።

በዚህ ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ካሊድ ሸረፋ እንደገለጹት ግብዓቱ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ለተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች የሚውልና ህይወት አድን የሚባሉ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ድጋፉን ላደረገው ኦርፋንስ ኢንኒድ ዩኤስኤ/Orphans in Need USA/ እና ለኡስታዝ አቡበከር አህመድ ምስጋና አቅርበዋል።

መሰል ድጋፎችን ማድረግ በቀጥታ የዜጎች ህይወት ላይ ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ ሆስፒታሉ ታካሚዎችን የተሻለ ለማገልገል የሚደረጉ መሰል ድጋፎችን ያበረታታል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም