ቀጥታ፡

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦ የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ማለዳ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያንና ለሀገር ሉአላዊነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች ታሪክን አስጎብኝተናል ብለዋል።


 

በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ እመኛለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም