ቀጥታ፡

የጽንፈኛው ሃይል አመራሮችና አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው መግባት ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦ የጽንፈኛው ሃይል አመራሮችና አባላት መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ በመቀበል መግባት መቀጠላቸውን በመከላከያ ሰራዊት የምስራቅ እዝ አስታወቀ። 

እዙ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው የሰላምን አማራጭ የተቀበሉት የቡድኑ አመራሮችና አባላት በጎጃም ቀጣና የሚንቀሳቀሱ ናቸው።

ለጥምር ጦሩ እጅ የሰጡት የጽንፈኛው ቡድን አመራሮችና አባላት መርዓዊ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
 



የቡድኑ አመራሮችና አባላት የገቡት 1 ፒ ኬ ኤም/መትረየስ ፣ 11 ክላሽ፣ 2 ኤስኬስ፣ 2 ፋል፣ 4 ቦንብ፣ 1 የመገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ የተለያየ መሳሪያ ጥይቶችንና ካዝናዎችን በመያዝ ነው።

በሰላም ከገቡትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙት 22 አመራሮችና አባላት መካከል አስር አለቃ ቻላቸው አስናቀ(ቻቻ) ፣ ቢኒያም ጋሻው፤ ጋሻው መኳንንት ፣ዘላለም አዱኛ ፣እንዳላማው ገብሬ እና ጋሻ ታደለ የተባሉ አመራሮች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም