ቀጥታ፡

በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በጥራትና ፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018(ኢዜአ)፦ በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር እና የመልሶ ማልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጥራትና ፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከካቢኔያቸው ጋር በመሆን በከተማው እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ የመልሶ ማልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት በክልሉ በቅንጅትና በቁርጠኝነት በተሰሩ ስራዎች የሚይቻል የሚመስሉ በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል።


 

በተገኙ ድሎች መዘናጋት ሳይታይ ዛሬም ለበለጠ ድል እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ይህ ቁርጠኝነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ከተማዋ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ታሪክና ቅርስ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሆኑንና ስራዎቹ ሀረር በስሟና ታሪኳ ልክ ከፍታዋን የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

ይህም የጎብኚዎች መዳረሻነቷንና ተመራጭነቷን የበለጠ ማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማትና የመልሶ ማልማት ስራዎቹ በርካታ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረጉንና የዜጎችን የስራ ባህል ጭምር መቀየሩን ነው የተናገሩት።

ለመጪው ትውልድም ጭምር መደላደልን በሚፈጥር መልኩ ታቅደው እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው አንስተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ባደረጉት ምልከታም ለስራው ስኬታማነት የሚያግዙ አቅጣጫዎችንና አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም