ቀጥታ፡

‎የኮሪደር ልማት ስራዎች በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018(ኢዜአ):፦ የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ እንደሚገኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት የኮሪደር ልማት አጠቃላይ ስራዎች እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ ናቸው ብለዋል።


 

በመልዕክታቸውም ዛሬ በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ምዕራፍ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተናል ሲሉ ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገር ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም