በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዳማ ከተማ አሸንፈዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዳማ ከተማ አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር፣ ሁዘይፋ ሻፊ እና ሳምሶን ቹቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ታምራት እያሱ ለፋሲል ከነማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ24 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አምበሉ ቢንያም አይተን በ61ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ31 ነጥብ አምስተኛ፣ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ20 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ቀን ላይ በተደረጉ የ20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ መቻልን 4 ለ 3፣ ባህርዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።