ቀጥታ፡

ቼልሲ እና በርንሌይ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቼልሲ እና በርንሌይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ በ4ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ቼልሲን መሪ አድርጓል።

ዚያን ፍሌሚንግ በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ለበርንሌይ አንድ ነጥብ አስገኝታለች።

የቼልሲው ዌስሊ ፎፋና በ72ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ሜዳ ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ45 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

በርንሌይ በ19 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌሎች ጨዋታዎች በርንሌይ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 ሲረታ  አስቶንቪላ እና ሊድስ ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም