የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2018(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት የእውቅና መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (ፒኦኤ)ን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ጉባኤውን በመዘገብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ ከየካቲት 4 እስከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት ሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ፣ 39ኛው የመሪዎች ጉባኤ፣ የጣሊያን አፍሪካ ስብሰባ መካሄዱን አስታውሰዋል።
በተጨማሪም በርካታ የጎንዮሽ ስብሰባዎች መደረጋቸውን አመልክተው፤ እነዚህን ጉባኤዎች የማስተናገድ ሀላፊነት የተሰጣቸው አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገነቡ ስራዎችን ማከናወናቸውንም ገልጸዋል።
ጉባኤዎቹ በስኬት መጠናቀቃቸውን ጠቁመው፤ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የተሻለ ስራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ ለጉባኤው ስኬት አስተዋጽኦ ለነበራቸው ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።
በዚህም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (POA)ን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ጉባኤውን በመዘገብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በመርሀ-ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigital