ቀጥታ፡

በገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2018 (ኢዜአ)፦  በገጠር ኮሪደር መርሃግብር የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ሀገራችን በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በምስራቅ ወለጋ ዞን ላይ እየተሠራ ያለው የመደ ጃለላ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ፤ ዘመናዊ የፀሐይ ኃይል መጠቀሚያ፣ የባዮጋዝ ሥርዓት፣ የእንስሳት በረቶች፣ መጸዳጃ ክፍሎች እና የምድረ ግቢ አረንጓዴ ስፍራዎች ሥራን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል።


 

ይህም ለማኅበረሰቡ ዘላቂ እና የከበረ አኗኗርን የፈጠረ ሥራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም