የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ እድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ እድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ ነው
አዲስ አበባ፤የካቲት 12/2018 (ኢዜአ)፡-ከነቀምቴ ከተማ በ6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብቻ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ እድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በሶርጋ ሀይቅ ላይ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ በአሁኑ ወቅት በ14 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ ይገኛል።
የፕሮጀክቱ ስራ በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
ከነቀምቴ ከተማ በ6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብቻ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ እድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ መሆኑንም ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመጥቀም በክልሉ ዘላቂ ቱሪዝምን የሚያበረታታ ይሆናል።