ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ቦዶ ግሊምት እና ባየር ሌቨርኩሰን ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11 /2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ማምሻውን ሶስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።

በአስፕማይራ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቦዶ ግሊምት ኢንተር ሚላንን ባልተጠበቀ ሁኔታ 3 ለ 1 አሸንፏል።

ሶንድሬ ብሩንስታድ ፌት፣ ጄንስ ፒተር ሃውግ እና ካስፐር ዋርትስ ሆግ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ፍራንቼስኮ ፒዮ ኤስፖዚቶ ለኢንተር ሚላን ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።



በሌላኛው መርሐ-ግብር ባየር ሌቨርኩሰን ከሜዳው ውጭ በፓትሪክ ሺክ ግቦች ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0 ረቷል።

ክለብ ብሩዥ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።



በጃን ብሬይዴል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሪስቶስ ዞሊስ፣ ኒኮሎ ትሪሶልዲ እና ራፋኤል ኦንዬዲካ ለብሩዥ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጁሊያን አልቫሬዝ፣ አዴሞላ ሉክማን እና የክለብ ብሩዡ ጆኤል ኦርዶኔዝ በራሱ ላይ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።


ክለብ ብሩዥ ሁለት ጊዜ ተመርቶ አቻ ወጥቷል።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ካራባግን 6 ለ 1 ረቷል።

የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም