የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዎልቭስ እና አርሰናል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በሞልኒው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ እና ፒዬሮ ሂንካፒዬ ለአርሰናል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሁጎ ቡዌኖ እና የአርሰናሉ ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በራሱ ላይ ለዎልቭስ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ከ2 ለ 0 መምራት አቻ የወጣው አርሰናል በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ ጥሏል።
በጨዋታው አርሰናል የተሻለ ብልጫ ነበረው።
የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 58 ነጥብ ከፍ አድርጓል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
ዎልቭስ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
ዎልቭስ በውድድር ዓመቱ ያሸነፈው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
የሁለቱ ቡድኖች የ31ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛር የተደረገው አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለበት የካራባኦ ዋንጫ ከመርሐ-ግብሩ ጋር በመገጣጠሙ ምክንያት ማስተካከያ ተደርጎበት ነው።