ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ኒውካስትል ዩናይትድ ካራባግን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ካራባግን 6 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በቶፊቅ ባህራሞቭ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አንቶኒ ጎርደን ሁለት በጨዋታ እና ሁለት በፍጹም ምት በአጠቃላይ አራት ጎሎችን አስቆጥሯል።



ማሊክ ታው እና ጃኮብ መርፊ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ኤልቪን ጃፋርኩሊዬቭ ለካራባግ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በጨዋታው ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል።

አራት ግቦችን ያስቆጠረው አንቶኒ ጎርደን የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።



ውጤቱን ተከትሎ ኒውካስትል ዩናይትድ ጥሎ ማለፉ የመቀላቀል እድሉን የበለጠ አስፍቷል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም