ቀጥታ፡

የቱርክዬ እና የኢትዮጵያን ታሪካዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ወሳኝ ምዕራፍ

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ ቢሆንም እንኳን ባለፉት 20 ዓመታት ግን ተጠናክሮ የቀጠለ ሆኗል።

ከኦቶማን ኢምፓየር ዘመን አንስቶ ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ወዳጅነታቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከንግድ እስከ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት አላቸው።

ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለየት የሚያደርጉ በርካታ ታሪካዊ ዳራዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቱርክዬ ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ ቀድማ ኤምባሲዋን ኢትዮጵያ ውስጥ የከፈተችው ተጠቃሽ ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዋነኛ የስትራቴጂካዊ አጋር ተደርጋ በቱርክዬ በኩል የምትታመን መሆኗ ወዳጅነታቸውን ይበልጥ መሠረት ላይ እንዲተከል ረድቶታል።

በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዙርያ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀዳሚውን ድርሻ ከሚወስዱ የውጭ ኢንቨስተሮች መካከል ቱርካውያን ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው። በተለይም በጨርቃጨርቅ እና በማኑፍክቸርንግ ዘርፍ ግንባር ቀደም ናቸው።

የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶዋን በትላንትናው ዕለት ያከናወኑት ይፍዊ ግንኙነትም የሁለቱ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ሀገራት ግንኙነትን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶዋን መካከል የተከናወነው ምክክር በምጣኔ ሀብት እና በምሥራቅ አፍሪካ ደህንነት ጉዳዮች ዙርያ ያተኮረም ሲሆን በተለይም የባሕር በር ለኢትዮጵያ ከሚያበረክተው ሁለንተናዊ ሚና እና አስፈላጊነት አንጻር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ይህም የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነትን በአስተማማኝ ጎዳና ወደ ፊት መራመድ የሚችልበት ታሪካዊ ዕለት ያደርገዋል።

የፕሬዝዳንቱ እና ልዕካቸው ይፋዊ ጉብኝት በወሳኝ የታሪክ ሰንሠለቶች ላይ ተመስርቶ የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ይጠበቃል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም