የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ መመረቅ የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ ወደፊት የሚያስፈነጥር ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ መመረቅ የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ ወደፊት የሚያስፈነጥር ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ መመረቅ የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ ወደፊት የሚያስፈነጥር ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ምረቃ ላይ ተገኝተዋል።
በዚው ወቅት እንዳሉት የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መመረቅ ከውጭ የሚገባውን ይተካል፣የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣ የፋብሪካዎችን የማጓጓዣ ወጪ ይቀንሳል ብለዋል።
በብዙ ነገሮች ራሳችንን እየቻልን ነው ያሉት አቶ ተመስገን፥ ሉዓላዊነታችንም በሁለንተናዊ መልክ ምሉዕ እየሆነ ነው፣ኢትዮጵያም ትገሠግሣለች ነው ያሉት።