ቀጥታ፡

የአርጆ ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካ በኢትዮጵያ በዘርፉ የኢንዱስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦ የአርጆ ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የተፈጨ ድንጋይ ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላት በኢትዮጵያ የዘርፉ የኢንዱስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፋብሪካው ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊ ጥሬ ግብዓቶችን እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን በማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ልማትን እንደምታሳድግ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም