ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቺልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቺልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቺልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬቲ ሃምፕተን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት፥ ከፋውንዴሽኑ ጋር በቀጣይ በጋራ በምንሠራባቸው የትኩረት መስኮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
እንዲሁም የነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።