የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ በምዕራብ ወለጋ ገንጂ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተሠራ የሚገኝ ነው።
ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፕሮጀክቱ ለትምህርት፣ የመንገድ ልማት፣ የጤና ተቋማት እና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታን የማነቃቃት አቅም አለው ብለዋል።
በጉብኝታችን ወቅት እንደተመለከትኩት የፕሮጀክቱ ፋይዳ በአንድ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ማኅበረሰብ የበለጠ ለልማት በማነሳሳት ከፍ ያለ ሚናውን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉም ገልጸዋል።