በተጠባቂው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11 /2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በስታዲዮ ዳ ሉዝ በተደረገው ጨዋታ ቪኒሺየስ ጁኒየር በ50ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ያስቆጠራት ግብ ሎስ ብላንኮሶቹን አሸናፊ አድርጓል።
ቪኒሺየስ ግቡን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የገለጸበት መንገድ ቢጫ ካርድ እንዲመለከት አድርጎታል።
ቪኒሺየስ የቤኔፊካው ተጫዋች ጂያንሉካ ፕሪስቲያኒ የዘረኝነት ቃል ተናግሮኛል በሚል ሜዳውን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ጨዋታው ለ10 ደቂቃዎች ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በድጋሚ ቀጥሏል።
ከክስተቱ በኋላ ጨዋታው በውጥረት የተሞላ ሆኗል።
በጨዋታው ሪያል ማድሪድ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎች በመፍጠር የተሻለ ነበር።
የቤኔፊካው አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪኒዮ የዳኛ ውሳኔ በመቃወም በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ የ 1 ለ 0 ወሳኝ ድል ተሳክቷል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ፒኤስጂ ሞናኮን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በሉዊስ ሁለተኛ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዴዚሬ ዱዌ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አሽራፍ ሃኪሚ ቀሪዋን ጎል ለፒኤስጂ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ፍሎሪያን ባሎጋን ለሞናኮ ግቦቹን አስቆጥሯል።
የሞናኮው አሌክሳንደር ጎቪን በ48ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሴርሁ ጉይራሲ እና ማክሲሚሊያን ቤየር ግቦች አትላንታን 2 ለ 0 አሸንፏል።
የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይደረጋሉ።