በሻምፒዮንስ ሊጉ ጋላታሳራይ ጁቬንቱስን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሻምፒዮንስ ሊጉ ጋላታሳራይ ጁቬንቱስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10 /2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ጋላታሳራይ ጁቬንቱስን 5 ለ 2 ረቷል።
ማምሻውን በራምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖኣ ላንግ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋብርኤል ሳራ፣ ዳቪንሰን ሳንቼዝ እና ሳቻ ቦይ ለጋላታሳራይ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቱን ኮፕማይነርስ ለጁቬንቱስ ግቦቹን አስቆጥሯል።
የጁቬንቱሱ ሁዋን ካባል በ67ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
በጨዋታው ጁቬንቱስ 2 ለ 1 መርቶ የነበረ ቢሆንም የካባል በቀይ ካርድ መውጣት ብልጫ እንዲውሰድ አድርጎበታል
ውጤቱን ተከትሎ ጋላታሳራይ ጥሎ ማለፉ የመቀላቀል እድሉን አስፍቷል።
ጁቬንቱስ ውጤቱን ቀልብሶ የማለፍ ከባድ ፈተና ይጠበቀዋል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ይካሄዳል።