ቀጥታ፡

በብልጽግና ፓርቲ አካታችና የተቀናጀ የልማት እቅድ እምቅ ሃብቶች እየለሙ የህዝብ ተጠቃሚነት እውን እየሆነ ነው

ሰመራ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- በብልጽግና ፓርቲ አካታችና የተቀናጀ የልማት እቅድ እምቅ ሃብቶች እየለሙ የህዝብ ተጠቃሚነት እውን እየሆነ ነው ሲሉ የአፋር ክልል  ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

ብልፅግና ፓርቲ  በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ምልክቱን  (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጊያ ክልላዊ መርሃ ግብር አካሒዷል።


 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፓርቲው አካታችነት ያለው አሰራር በመተግበር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት ማሳተፍ  ያስቻለ ነው።

በተለይም እንደ አፋር ክልል የልማት አቅሞች የተለዩበትና ድሎች የተመዘገቡበት አመራር በመስጠት በተግባር ያረጋገጠ ፓርቲ መሆኑንም ተናግረዋል።


 

ከፋፋይነት እንዲቀርና አካታችነት ያለው ሰርዓት እንዲገነባ ሚናውን እየተወጣ የመጣ ፓርቲ መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያረጋገጡት።

ፓርቲው ሰላም፣ ልማትና እኩልነትን በማስቀደም መተግበሩን አብራርተው በአፋር ክልል በተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም መልማት መቻልና ተጠቃሚነትን ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ አጋርነትን  በማስቀረት እኩል ውሳኔ ሰጭነትን ተግባራዊ ያደረገ ፓርቲ ነው ብለዋል።


 

ፓርቲው በየደረጃው ውጤታማ ስራዎች እየሰራ መምጣቱን ገልፀው የራሰን አቅም በማሳደግና ልማትን በማረጋገጥ ተጠቃሚነትን ያስገኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዘንድሮ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግናን መምረጥ የተመዘገቡ የልማት ድሎችን ማሰቀጠልና ውጥኖችን ግብ ማድረስ እንደሆነም ተናግረዋል።

ፓርቲው ዛሬ ባካሔደው የምርጫ ምልክቱን (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ  የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ደጋፊዎቹ ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም