ቀጥታ፡

የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናል-‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ እና የቱርክዬን ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናል ሲሉ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶጋን ጋር ዘለግ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።


 

ውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ ትብብር ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በስትራቴጂካዊ የትብብር መስኮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናልም ነው ያሉት።


 

ዘላቂው ግንኙነታችን ሁለቱ ሀገሮችን የሚያስተሳስረውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም