የተለያዩ ጉዳዮችን በመወያየት በሰፋፊ እድሎቻችን እና ትብብሮቻችን የተመሠረቱ ተጨባጭ ዘላቂ ልማቶችን መቀየስ እንችላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ ጉዳዮችን በመወያየት በሰፋፊ እድሎቻችን እና ትብብሮቻችን የተመሠረቱ ተጨባጭ ዘላቂ ልማቶችን መቀየስ እንችላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡-በሀገሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውን ቡና በጋራ እየቀመስን የተለያዩ ጉዳዮችን በመወያየት በሰፋፊ እድሎቻችን እና ትብብሮቻችን የተመሠረቱ ተጨባጭ ዘላቂ ልማቶችን መቀየስ እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይፕ ኤርዶዋን፤ መቼም ቢሆን እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ልብ ወዳጅ ሀገሬ ለእርስዎ የምታደርገውን ደማቅ አቀባበል ከእርስዎ ጋር ለመካፈል በመቻሌ ክብር ይሰማኛል ብለዋል።
በሀገሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውን ቡና በጋራ እየቀመስን የተለያዩ ጉዳዮችን በመወያየት በሰፋፊ እድሎቻችን እና ትብብሮቻችን የተመሠረቱ ተጨባጭ ዘላቂ ልማቶችን መቀየስ እንችላለን ሲሉም ገልጸዋል።