ቀጥታ፡

በዲጂታል ልማት የኢትዮጵያ ዕድገትና ማንሠራራት በተግባር እየታየ ነው

አክሱም፤ የካቲት10/2018 (ኢዜአ)፡- በዲጂታል ልማት የኢትዮጵያ ዕድገትና ማንሠራራት በተግባር እየታየ መሆኑን በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

በዩኒቨርሲቲው የኮምፒውተር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ሀፍቶም መኮንን፤ በዲጂታል ልማትና ትግበራ ኢትዮጵያ ወደ ፊት የተራመደችባቸው በርካታ ማሳያዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።
 
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂክ ትግበራ የታዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችና የተመዘገቡ ውጤቶች አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ለውጥ ማምጣታቸውንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የዲጅታል ትግበራ በዘርፉ ዕድገትና ማንሠራራት የታየበት ስለመሆኑ በትክክል መግለጽ ይቻላል ሲሉም ለኢዜአ ተናግረዋል። 



 
በዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምህር ተኽላይ ምሩፅ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት የእስካሁኑ ትግባራ በጣም ብዙ ለውጥ የተመዘገበበትና የቀጣዩ ዕቅድም ተስፋ የተሰነቀበት መሆኑን ገልጸዋል።
 
የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ ለመክፈት በመንግሥት እየተደረገ ያለው ዕቅድ ለዘርፉ ልማት መሳካት መሰረት የሚያኖር መሆኑን ገልጸው፤ ለስኬቱ የሁላችንም እገዛ ያስፈልጋል ብለዋል። 
 



ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የስኬት ተሞክሮ በመነሳት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የላቀ ውጤት በጋራ መትጋት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዘቡት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምህር መድሃንየ ካሓሳይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም