ቀጥታ፡

ምርጫ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ልምምድን የሚያጠናክሩበት መንገድ ነው

ዲላ፤ የካቲት 10/2018 (ኢዜአ):- ምርጫ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ልምምድን የሚያጠናክሩበትና ሀገርን ለማጽናት ትክክለኛ መንገድ መሆኑን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አስገነዘቡ።


 

በዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና ሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ደሳለኝ አያሌው እንዳሉት፤ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያቀርቧቸው አማራጭ ሐሳቦች አማካኝነት ዜጎች የዴሞኪራሲ መብታቸውን ተጠቅመው መሪዎቻቸውን የሚመርጡበት ትክክለኛው መንገድ ነው።


 

ምርጫ የምንፈልጋቸውን መሪዎች በነጻነት በመምረጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሥርዓተ መንግሥትን የምናስቀጥልበትና ዴሞክራሲያዊ ልምምድን የምናጠናክርበት ነው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱ ሀሰን (ዶ/ር) ናቸው።

በመሆኑም ዜጎች በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ በመሆን መሪያቸውን የመምረጥ መብታቸውን ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ምሁራኑ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም