ቀጥታ፡

ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው- ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ

ጅግጅጋ፤  የካቲት 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልፅግና ፓርቲ  በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ገለጹ።

የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶውን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለህዝቡ አስተዋውቋል።


 

በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ የዜጎችን እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት እውን ማድረግ የቻለ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ቀርቶ እኩል ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት የተረጋገጠበት፣ በሀገሩ ጉዳይ ሁሉም ያገባኛል ብሎ የሚሰራበትና የመሪነት እድል የሚያገኝበት አካታች የዴሞክራሲ ስርአት መፍጠሩን ተናግረዋል።

ፓርቲው በተለይም በሶማሌ ክልል ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እንዲከናወኑና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት የሚጨበጥ ውጤት ስለማስመዝገቡም ገልጸዋል። 


 

በመሆኑም በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን መምረጥ፣ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የህዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ  አስረድተዋል።

በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ደጋፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም