የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማምሻውን ተከናውኗል።
በዚሁ መሰረት ማንስፊልድ ታውን ከአርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ፣ ዎልቭስ ከሊቨርፑል እና ሬክስሃም ከቼልሲ ይጫወታሉ።
ሊድስ ዩናይትድ ከኖርዊች ሲቲ፣ ፉልሃም ከሳውዝሃምፕተን፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከማክስፊልድ እና ብሬንትፎርድ አሸናፊ እንዲሁም ሰንደርላንድ ከፖርት ቫሌ እና ብሪስቶል ሲቲ አሸናፊ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር መርሐ-ግብር የካቲት 28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።