ህዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወርን የዘወትር መልካም ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ ይገባዋል - ኢዜአ አማርኛ
ህዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወርን የዘወትር መልካም ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ ይገባዋል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር የዘወትር መልካም ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የታላቁ ረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙኃን የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የረመዳን ጾም ህዝበ ሙስሊሙ መልካም የሆኑ ተግባራትን በማከናወን የሚያሳልፉት የጾም ወቅት ነው ብለዋል፡፡
ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች መካከል የረመዳን ፆም አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ወሩ ኃይማኖታዊ ስርዓት የሚከናወንበት ነው ብለዋል፡፡
የዘንድሮው የ1447ኛውን የታላቁ ረመዳን ወር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በሚያሳውቀው መሠረት የጾሙ የመጀመሪያ ዕለት የጨረቃ መታየት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
በዚህም መሠረት ጨረቃ ነገ ማክሰኞ ምሽት ከታየች፣ የመጀመሪያው የጾም ቀን ረቡዕ ይሆናል፤ ጨረቃ ማክሰኞ ምሽት ካልታየች ደግሞ፣ ጾሙ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጸዋል።
ለህዝበ ሙስሊሙም ለታላቁ የረመዳን ጾም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።